Printed Book
የደቀ መዝሙርነት ጽኑ መሠረት
የደቀ መዝሙርነት ጽኑ መሠረት
About This Book
የደቀ መዝሙርነት ጽኑ መሠረት - አምድ አንድ | ሥር-ነቀል ደቀመዝሙርነትን ማቀጣጠል
የደቀ መዝሙርነት መጽሐፍት በአምድ ተከፍለው ቀጣይነት ያላቸው እና ተከፋፍለው የታተሙ ሲሆን በእያንዳንዱ አምድ ውስጥ አስር ምዕራፎች የሚገኙ ሲሆን በእያንዳንዱ መፅሐፍ ውስጥና ከመፅሐፍ ወደ መጽሐፍ ሚኖረው የሐሳብ ፍሰት ውበትና ጥልቀት ያለው እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ ከእውቀት ከባሕርይ ከክህሎትና ከስልት አንጻር ደቀ መዝሙር በመሆንና በማድረግ ሂደት አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ መርሆዎች ጉልህ ስፍራ ተሰጥቶአቸዋል። የትምህርት አሰጣጡ ተማሪዎች ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አካሄድ የሚከተል ሲሆን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ጥያቄዎች ተዘጋጅተዋል።
የደቀ መዝሙርነት - አምድ አንድ መፅሐፍ የራሱ የአነባብ እና አጠቃቀም መመሪያ ያለው ሲሆን በውስጡም ስለ አዲስ ሕይወት ፣ በቃሉ የታነፀን ሕይወት መምራት ፣ ጸሎት ፣ እውነተኛ አምልኮ ፣ በቤተክርስቲያን መታቀፍ ፣ የጸጋ ስጦታን መጠቀም ፣ መንፈሳዊ ውጊያ ፣ ጋብቻ እና ክርስቲያናዊ ቤተሰብ ፣ በመስጠት ውስጥ መሠጠት እና ፍሬያማነት የሚሉ ንዑስ ርዕሶች ያካተተ ነው።
በዚህ አምድ አንድ በክርስትና ጉዞአችን እጅግ መሰረታዊ በሆኑ እውቀቶች ላይ ጽኑ መሰረት እንዲኖረን በሚረዱን ትምህርቶች ላይ ቀዳማዊ ትኩረት ተሰጥቷል። የመጽሐፍ አጠቃቀሙም መከተል በሚገባን ነጥቦች መንፈሳዊ የሕይወት መመዘኛ ፣ አጠቃላይ ዕይታ ፣ የእግዚአብሔር ቃል/የመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል ፣ የመወያያ ጥያቄ ፣ ተግባር ተኮር የቤት ሥራ ፣ የቃል ጥናት ጥቅስ እና ጸሎት ተብራርቶ ተቀምጧል።
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ደቀ መዝሙርነት እና የቤተክርስቲያን ትምህርት መምሪያ ክፍል አዘጋጅቶ እና አሳትሞ ያቀረበ ሲሆን ከወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ መፅሐፍ ስርጭት ቢሮ በመሄድ ማግኘት ትችላላችሁ።
Interested in This Book?
Contact us to ask about availability and how to get a copy.
+251 916 125033