አባባ ዋንዳሮ የወላይታ የመጀመሪያዉ የወንጌል አርበኛ
ሙሉ ስሙ አባባ ዋንዳሮ ዳባሮ ይባላል። አባባ ዋንዳሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ደቡብ አቅጣጫ 20 ኪ.ሜ በምትርቅ ሁምቦ በምትባል ወረዳ በ1906 ዓ.ም ተወልደዋል። ዋንዳሮ የእግ/ር ጥበብ ሕያዉ ምስክር ነዉ። ከዉጭ የሚታይ ምንም ዓይነት የተለየ ባሕርይ ስለሌዉ ሰዎች መሪ ይሆናል ብለዉ አይገምቱትም። ሆኖም “ሰዉ ፊትን ያያል፣ እግ/ር ግን ልብን ያያል“ ፤ ሰዎች ያልተስተካከለ ጥሬ ዲንጋይ ሲያዩ እግ/ር ግን የከበረ እንቁ አየ። የራሱ የዋንዳሮ ምስክርነት ማንነቱንና ጥቅሙን ያረጋገጠ በመሆኑ፣ የሰዎች ግምት ስተት ሆኖ ቀረ። አባባ ዋንዳሮ ሚስዮናዊያንን የተገናኘበትን እና ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበለበትን አጋጣም ሲያስታዉስ እንዲ ይላል፡-
‹‹በአንድ ቀዝቃዛና ብርዳማ ቀን ገና ፀሐይ ሳትወጣ እሑድ ገበያ ለመሄድ ከቤቴ ወጥቼ ስጓዝ ኦቶና ከነጮች መንደር ደረስኩኝ። መንደሩን በሚያቋርጠዉ መንገድ ሳልፍ በአንድ በልዩ ዓይነት ቤት አጠገብ ቆሞ የነበረ አንድ ነጭ ሰዉ ጠራኝ። ሌሎች ወላይታዎች አብሮዎት ቆሞዋልና መሄዱ አደጋ የሌለበት መሆኑን ገምቼ ተጠጋዉ። ዉጪዉ በጣም ቀዝቃዛና ይሚዘንብ ስለ ነበረ ፣ ሁላቸንም ወደ ትንሽ የሣር ቤት ዉስጥ እንድንገባ ተጋበዝን። በቤቱ ዉስጥ ነጮች ካከማቹት መድኋኒት የተነሳ እንግዳ የሆነ ሽታ ነበር። ነጩ ሰዉ በመካከላችን ሆኖ በወለሉ ተቀመጥን። እርሱም ጢም የለሌዉ፣ ፊቱ የገረጣ፣ ልብሶቹም እንግዳ የሆነ ለግላጋ ወጣት ነበረ። ቋንቋችንን በደንብ ባይችሉም፣ የሚናገረዉን ስለ ወደድኩ አዳመጥኩ። በኋላም ከሰባት ቀናት በኋላ እንድንመጣ ጋብዞን እኔም ለመሄድ ተነሳዉ።
እንደገናም ነጩ ወጣት ኢየሱስ ስለ ተባለዉ ሰዉ ሲናገር ሰማዉ። ይህ ሰዉ ወደዚህ ዓለም በእግ/ር የተላከ ሲሆን፣ እርሱም ድንቅ ሥራዎችን አከናዉኗል ሲል ነገረን። ነጩ ወጣት በእጁ የያዘዉን መጽሐፍ እግ/ር እንደሰጣቸዉና እግ/ር በእዚህ መጽሐፍ ዉስጥ ማንም ሰዉ(ወላይታም) ጭምር ለሃጢያቱ ይቅርታ እንዲሁም በልቡ ሰላምን ቢፈልግ የኢየሱስ ተከታይ በመሆን ሊያገኝ ይችላል እንደሚል ነገረን። ለሁሉም ይህ በዉስጤ እንደ ማር ስለ ጣፈጠኝ ደግሜ መምጣትና ይበልጥ መስማት እንዳለብኝ አሰብኩ።
ከሰባት ቀናት በኋላ እንደገና ኦቶና መጣዉ። ነጭ ሰዉ እኛ ብዙ መጥፎ ነገሮችን በመስራት እግ/ርን ያስቆጣን መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ ተናገረ። እርሱ ይቅርታ እንዲያደርግልና ኀጢያታችንን እንዲውስድልን እኛ በኢየሱስ ማመን አለብን ካለ በኋላ በቀጥታ ወደ እኔ በማመልከት ማመን እንደምፈልግ ቢጠይቀኝም፣ አባቴ ጠንቋይ እንደ ሆነ ነገርኩት። አባቴ በራሱና በሁምቦ ተራራ አከባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ(መጥፎ) መንፈሳዊ መሪ ነበረ። ›› ዋንዳሮ ወንጌልን ለሦስተኛ ጊዜ ከሰማ በኋላ ልቡን ከፈተ፣ ራሱንም ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳልፎ በመስጠቱ ሕይወቱ ወዲያ ተለወጠ። ማንበብን መማር ቢፈልግም፣ የነበረዉ መጽሐፍ ቅዱስ በአማረኛ ቋንቋ ብቻ ነበረ። አማረኛ ብሔራዊ ቋንቋ ይሁን እንጅ በወቅቱ የነበረው አብዛኛው የወላይታ ሕዝብ አያዉቀዉም ነበር።
ሚስስ ሉዊስ ብዙ ወጣት ክርስቲያኖችን ማንበብን አስተምራለች። ዋንዳሮ ግን የአማረኛ ፍደሎችን መያዝና መረዳት ባለመቻሉ ሚስስ ሉዊስ ብዙ ለፋች። ከክፍል ጓደኞች ወደ ኋላ በመቅረቱ፣ እርሱም ተስፋ ቆረጠ። ሚስስ ሉዊስም ታምማ ለረጅም ጊዜ ውሎዋ በመኝታ ክፍሏ ሆነ። ለዋንዳሮ ካላት ሐሳብ የተነሳ በሳምንት ሦስት ጊዜ ለይታ ልታስተምረዉ ጀመረች። ሁልጊዜም አንገቱን ዝቅ አድርጎ እግ/ር ተጨማር ፊደል ለመማር እንዲረዳዉ ሲጸልይ ታስተዉለዋለች። በመጨረሻ፣ ትምህርቱ ግልጽ ሲሆንለት፣ የምስጋና ጸሎት በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ያደርጋል። በአንድ ቀን አንዲት ፊደል እንኳን በደንብ ተምሮ ሲያዉቅ በዚህ ደስ ይለዋል።
ከሚስስ ሉዊስ ትዕግስት ከተሞላበት እርዳታ የተነሣ ዋንዳሮ አማረኛን በደንብ ባያቀላጥፍም፣ በጥሩ ሁኔታ ማንበብ ቻለ። አንድ ቀን ዋንዳሮ በእሁድ የአምልኮ ፒሮግራም ላይ እንዳለ ተነስቶ ለመናገር አስፈቀደ። በዚህ ንግግሩ ወንጌልን ለመስማት የሚመጣዉ ሕዝብ ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ስብሰባዉ ከሚካሄድበት የሚስዮኑ ክልኒክ ሕንጻ ከአቅም በላይ በመሆኑ ፣ ቤት ተጋግዞ እንደሚሰራዉ ሁሉ ፣ እግ/ር የሚመለክበትን ቤት በአንድነት መሰራት እንዳለበት ጠቆመ። ጥቆማዉ በአማኞች ተቀባይነት አግኝቶ በሚስዮኑ ጣቢያ አጠገብ በተመደበዉ ቦታ ቀን እርሻቸዉን እየሰሩ ከሰዓት ዘግየት ብሎና ማታ ቤተክርስቲያን መስራት ጀመሩ። ቤቱ የሚሰራዉ እንደ አብዛኞዎቹ የሚስዮኑ ቤቶች ከጭቃ በተሰሩ ጡቦች ነበር። ሚስዮናዉያንም በኩራዝና በፋኖስ መብራት ሥራዉ ሲሄድ አብረዉ በእጃቸዉ በመስራት ይረዷቸዉ ነበር። ማታ ማታ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አከባብ ሴቶች ቡና አፍልቶዉ ከቦቆሎ ቆሎ ጋር ያመጣሉ። ይህም ከተበላና ከተጠጣ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተካሂዶ ሰዎች ወደየ ቤታቸዉ ይሄዳሉ።
አንድ ቀን ማታ በእሳት ዙሪያ ተቀምጠዉ ልምዳቸዉን ሲያክፍሉ፣ ዋንዳሮ እንደት ሊያምን እንደ ቻለና ዉጠቱንም ይነግራቸዋል። ‹‹እዉነት ነዉ የምላችዉ ያኔ ያደረኩት እስካዉን አይገባኝም። በቆምኩበት ጊዜ እግ/ርን ማመንና የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን መፈለገ ከዉስጥ ሲገለጽልኝ በእኔ አንድ ነገር ሆነ። ከዚያ ጊዜ አንስቶ እስካዉን ልቤ በደስታ ተሞላ፣ አይቸዉ የማላዉቀዉ አዲስ ሰላምም በዉስጠ ሰፈነ። በኋላ ሌሎቸም አመኑ ብዙ ሰዎች በሳምንቱ ቀናት ሁሉ ከሁምቦ እስከ ሶዶ ከእኔ ጋር ይመላለሱ ነበር። ፈረንጁ ሰዉዬ እኛ ከፈለግን ወደ ምንኖርበት መንደር መጥቶ ለተወሰነ ጊዜ ከእኛ ጋር ለመቆየትና ስለ ኢየሱስ የበለጠ ለማስተማር ፍቃደኛ መሆኑን አስታወቀ። በዚያን ጊዜ የሁለት ዓመት ልጄ ታመመ። ጠንቋዩ አባቴ ልጁ የታመመዉ እኔ የአባቴን ሀይማኖት ስለተዉኩ መሆኑን ገልጾ ወቀሰኝ።
እኔ የቤተሰቦቸን ጣኦት ትቼ ኢየሱስን የተባለ አዲስ አምላክ መከተለ ስለ ጀመርኩ አሁን ደግሞ ኢየሱስን ክጄ ወደ ቤተሰበቸንና የጎሳችን እምነት ተመልሼ እንደገና ለሰይጣንና ለሎችም ርኩስ መናፍስት መሥዕዋት ካላቀረበዉ የታመመዉ ልጄ እንደሚሞት አረጋገጠ።ይህም ባከባቢ ባሉ መንደሮች ሁሉ ተነገረ፣ታወቀ። ነገር ግን አንድ በእኔ ዉስጥ ያለ ድምፅ ይህንን እንዳላደርግ እንደ ቀድሞ አያቶቼ፣ ሰይጣንና ርኩስ መናፍስትን ወደ ማምለክ አንዳልመለስ ይመክረኛል። ስለዚህም ለርኩስ መናፍስት መሥዕዋት አላቀርብም ፣ በእኔ ወይም በልጄ ላይ ምንም ነገር የሚደርስ ቢሆን ይህንን አላደርግም ብየ ነገርኩት። ከጥቅት ጊዜ በኋላ ልጄ ሞተ። በባህላችን መሠረት ለቅሶና ዋይታ የመጡ ሰዎች ፊታቸዉን መቧጨርና መቆራረጥ፣ደረታቸዉንም መምታት ጀመሩ። እኔም ይህን እንዳያደርጉና እንዲያቆሙ እኔ ራሴ ምንም የማላማርርና የማላዝን ስለ ሆንኩ እነርሱም እንዳያለቅሱ አጥብቄ ነገርኳቸዉ። እርግጥ ነዉ የልጄ ሞት ለእኔ ትልቅ ጉዳት በመሆኑ ተሰምቶኛል።
ነገር ግን በዉስጤ ከፍተኛ ሰላምና የደንነት ስሜት ስላለ ፣ እነርሱ እንዲያለቅሱ አልፈለኩም። ባለቤቴ ገና ወጣት ሴት ነበረች። እርሷም በሰይጣንና በማያምኑት አምልኮ ሥራዓት ተዉጣ ስለ ነበረ ዋይታና፣ ፊቷን መቧጨሯንና ሎችንም ማድረግ ቀጠለች፣ እግ/ርንም ሰደበች። የምታደርገዉን እንድታቆም ስነግራት በጣም ተቆጣች። ለቅሶዉ ከሰባት ቀን በኋላ ሲያበቃ ትታኝ ወደ ወላጆችዋ እንደ ምትሄድ ነገረችኝ። ለቤተሰቤ ፍቅር የሌለዉ ከመሆኑ የተነሳ ለአባቱ ጣኦት መሰዕዋት አቅርቦ የራሱን ልጅ ሕይወት ለማዳን ከማይፈልግ ሰዉ ጋር መኖር እንደማትችል ከገለጸች በኋላ ቤቱን ለቅቃ ሄደች። ከዚያን ወዲህ ለብዙ ጊዚያት ይህ ነጭ ሰዉ ከእግ/ር መጽሐፍ የሚያነብልን ቃል እዉነት መሆኑን አረጋግጫለዉ። እርግጥ ነዉ የዚህን ዓለም እዉቀት ያልተማርኩ ተራ ወላይታ ነኝ፣ ቢሆንም ከመጽሐፉ የተማርኩት የእግ/ር ቃልና ኢየሱስን መከተለ በዉስጤ ሰላምን አይፈጥርም ብሎ ሊያስተምረኛ የሚቃጣ የለም፡ እግ/ር ሃጢያቴን ይቅር እንዳለልኝና ልጁ እንዳደረገኝ በልቤ አዉቃለሁ።››
በዋንዳረሮ ሕይወት የተከሰተዉን ለዉጥ ተመልክታ ባለቤቱም ወደ እርሱ ተመለሰች። ያሁን መልካም ጠባዩ ከድሮ የተለየ በመሆኑ ትቀርበዉ ታዳምጠዉና ለእርሷም ሆነ ለላዉ ሁሉ የሚመሰክረዉን መልእክት አመነች። አብረዉም በታማኝነት ጌታን ለብዙ ዓመታት አገልግለዋል።
Share This Article